أبراهم إدغة אברהם אדגה አብራሐም : አድገህ ።

የሐይፋ : ታሪክ᎗ ከአቶ: አብራሐም : አድገህ ።

לקריאת הסיפור של אברהם אדגה בעברית, הקליקו כאן

ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ሐይፋ ከተማ ታሪክ ከሌሎች ደራሲወች ጋር ሁኘ እንድጽፍ መልእክት ሲደርሰኝ  እንግዳ ሆኖ ታይቶኝ ነበር። ከትቂት ጊዜ በኋላ ግን  ከደራሲዏች ጋር መተዋወቅ  ስጀምር ሌሎች ባልደረቦቸም ከኔ የበለጠ እውቀት ወይንም ልዩ ሚስጥር የማያውቁ መሆናቸውን ተረዳሁት ። ቀስበቀስም ከእለት እለት የሙማ ድርሻየ ምን እንድሆን አወቁ ። ከዚያም ከዚህ በታች ያቀናበርኩትን ድርሰት ለአንባቢያን ለማቅረብ በቃሁ ።

ወላጆቸ ዕድሚያቸውን ከጤና ጋር ፈጣሪ አምላክ ያስረዝመው  እንጅ ፡ብዙ ትችቶችን፤ ታሪክና ምሳሌወች ፤ ምክር አዘል ትንቢቶችን ገና ትንሽ ልጅ እያለሁ ያስተምሩኝ ነበር ።"ቤት ዘጠኝ እንጅ ዓስር አትሞላም "። ምንም ቢሟላልህ ሁል ጌዜ ያነሰህ ነው የሚመስልህ እያሉ ይተቹት የነበረው አሁን እውን ሁኖ አገኝሁት ። ከዚያ ሌላ ደግሞ " ብትከፋ ፤ ደስተኛ ብትሆን፤ ብትራብ ፤ ብትጠማ  ቤት ገመና ከዋኝ ናት"  እያሉ ይናገሩት የነበረውንም ከራሴ ላይ ደርሶ አገኘሁት።

ይህ ሁሉ እንዴት ባለ ሁኔታ ከሐይፋ ታሪክ ጋር ተገናኘ ? ለሚለው ጥያቄ ፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በፊት ብዙወቹ  የሐይፋ ከተማ ነዋሪወች አረቦች ነበሩ። ከነዚህ አረቦች መሃከለም አንዳዶቾቻቸው ሃብትምና ባለመብት  ነበሩ። በዚህም አጋጣሚ፡ ሃብታቸውን እና ያላቸውን መብት በመጠቀም አስደናቂና ደስ የሚሉ ትላልቅ ህንጻ ቤቶች ያሰሩ ነበር። ከነዚህም ፡አንዱ  ቲቬሪያ ጎዳና 15 በመባል ፡ይታወቃል።

ይህ ቤት የተሰራው የአውሮፓ ፡ይሁዲያውያን ይኖሩ የነበረበትን ሐገርና  የስራ ልምድ ትተው  ወደዚህ ስደት በጀመሩበት ወቅት ነበር። ወቅቱም አሰቃቂና አሳዛኝ ነበር ።በዚያን ወቅት ወደዚች ሐገር ለመምጣት የሞከረ ይሁዲያውያን  የእንግሊዝ ቀኝ ግዛት አስተዳዳሪወች እየያዙ እስር ቤት ከማስገባታቸው  ሌላ ገና በባሃር ላይ እያሉ አድነው በመያዝ ወደመጡበት እንዲመለሱ ያስገድዷአቸው ነበር ። እነኝህ ተገደው ይመለሱ የነበሩትም በመንገድ ላይ ወይንም ተመልሰው ወደ አውሮፓ ሲደርሱ በጨካኝ የናዚ እጅ በመውደቃቸው ወደ ይሁዲያውያን መሰብሰቢያ ቦታ ከተላኩ በኋላ መጨረሻ ላይም ተጨፍጭፈው በማለቅ ለዘርም ሳይበቁ ቀርተዋል ።

ከዚህ አደጋ ድነው እንደማንም ብለው ከመርከብ ወርደው ከሃይፋ ከተማ ለመድረስ  የበቁት ደግሞ፤ ከለበሱት ልብስ ሌላ ለእለት ወደ አፋቸው የሚያስገቡት ምግብ ወይንም ከዝናብ እና ከፅሃይ የሚጠለሉበት ቤት ስለአልነበራቸው ከነዚህ ነባር አረቦች ተጠግተው የቀን ሰራተኛ በመሆን ኑሮአቸውን መጋፋት ጀመሩ ። በዚህ ምአጋጣሚ   ቲቬሪያ ጎዳና 15 በመባል የሚታወቀው ቤት በነዚህ ባለሙያወች ተሰራ።

 በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከስድስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ይሁዲያውያን አሰቃቂ በሆነ መንገድ ተገደሉ። ከዚያም  የተባበሩት የዓለም መንግሥታት ይሁዲያን እራሳቸውን ችለው እሚኖሩባት ሐገር ተሰጥተው ኑሮአቸውን እንዲጀምሩ ውሳኔ ላይ ደረሱ  ። ይህ ውሳኔም በ 1948 እውን ሁኖ ከዚህ ይኖሩ የነበሩትም ሆነ ገና ከውጭ ያሉት በደስታ ተሞሉ። ደስታውም በጣም በአጭር ጊዜ ትልቅ መከራ ሁኖ ተገኝ። ምክኒያቱም ከዚህ ይኖሩ የነበሩ አረቦች ይህን አዲስ መጥ ህዝብ በሰላም ተቀብለው ሐገሪቱንም በዓለም መንግስታት አማካኝነት ተከፋፍለው ለመኖር ፍቃደኛ ስላልነበሩ ወዲያውኑ ጦርነት ጀመሩ።

ይህ የነፆነት ጦርነት በመባል የሚታወቀው ፊልማ በብዙ የታሪክ መዝገቦች ላይ ስፍሮ ይገኛል ። ከሌላው ጦርነት ፊልማም ለየት የሚያደርገው እነኝህ ነባር አረቦች ሌላ የጎሪቤት ሐገር ወገኖቻቸውን በመሰብሰብ አልሞት ባይ ተጋዳይ ከነበሩት ቁጥራቸው ትንሽ ከነበሩ ይሁዲያውያን ጋር ተፋልመው መሸነፋቸው ነው። ሲሸነፉም ይኖሩ የነበሩበትን ቤትና ንብረት እየተው ወደ ጎሬቤት ሐገር በመሄድ ስደተኛ ሆኑ። ይህ ቲቬሪያ ጎዳና 15 በመባል የሚታወቀው ቤትም እንዲሁ የቤቱ ባለቤት የመኖሪያ ቤቱን ትቶ በመኮብለሉ  አዲስ መጥ ይሁዲያውያን ተረክበውት መኖር ጀመሩ ። ቤቱም በውበቱ አስደናቂ በመሆኑ ከዚያም ሰፊና ለብዙ ቤተሰብ የሚበቃ በመሆኑ አዲስ መጦች ውስጡን በመከፋፈል የተለያዮ ሰወች ከዚያን በፊት የማይተዋወቁ በአንድ ላይ ይኖሩበት ነበር። በአሁኑ ወቅት ቤቱ ማትናስ በመሆን በአካባቤው የሚኖሩትን በሙሉ ሲያገለግል ይገኛል ።

ለምን ስለዚህ ቤት ለመጻፍ ወሰንኩ፤ ለሚለው ጥያቄ ። አንደኛ ይህ ቤት ብቻ ሳይሆን ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ቤቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ተለቀው በአዲስ ገቢወች እጅ ተይዘው ይገኛሉ። እነዚህ ቤቶችም ሆነ  ሌላም ወደ ኋላ እየተውት የሮጡት ንብረታቸው እንዲመለስላቸው አረቦች ጥያቂ ከማቅረብ ተቆጥበው አያውቁም። ሌላም ደግሞ ሃይፋ ከተማ  አረቦችና ይሁዲያውያን በሰላም ይኖሩባታል በባል ታዋቂ ናት ። ይህስ እውነት ነው ወይንስ ፡እንዲሁ ሰወች የልባቸውን ምኞት እውነት አስመስለው ስለሚናገሩ ይሆን የሚለለው ጥያቄ ሁል ጊዜ ይጎተጉተኝ ስለነበር ስለሁኔታው የሚያውቁ ባልደረቦቸ ጋር ስገናኝ ከነርሱ በቂ ማስረጃ አገኝ ይሆናል የሚል እምነት ስለአደረብኝ ሁኔታው ገፋፍቶኝ መልስ ለማግኘት ተነሳሁ።

በንብረቱ የተነሳ ስመለከተው በርግጥ ሰው ከተወለደበት ቦታ ተፈናቅሎ  ስደተኛ ሲሆን በጣም ያሳዝናል ። ሆኖም ግን በጦርነት ሜዳ ተሰልፎ ከተቸነፉ በኋላና  ለብዙ ዘመናት ከቦታው ከጠፉ በኋላ እንደገና  ያን የነበረውን ሃብት መልሱልኝ ማለቱ ከእውነት የራቀ ነው። ምንም እንኳ ምክኒያቱ ተመሳሳይ ባይሆንም ወላጆቸም ሃብት ንብረታቸውን ትተው ከመጡ በኋላ እንደገና መልሱልኝ የሚል አቤቱታ ወይንም ዛቻ አላሰሙም ።ለወደፊቱም የዚህ ዓይነት አቤቱታ ቢያቀርቡ በበጎ ዓይን ሳይሆን በጥላቻ ዓይን የሚመለከታቸው እንደሚበዛ እርግጠኛ ነኝ ። ሆኖም ግን ከጎናችን አብረውን የሚኖሩትን ግን እንደሁሉም ዜጋ መብታቸው እና ግዴታቸው ተመሳሳይ መሆን ይገባዋል።

ሃይፋ በተፈጥሮ ውበት የታደለች ከተማ ናት ። ከተራራው የተሰሩት ቤቶች  ጥዋት በምስራቅ ፀያይ ጮራዋን ስትዘረጋም ሆነ ምሸት በምዕራብ ስትገባ ውሃውን በልዩ  ቀለም ስትቀባው ማየቱ ብቻ ከበሽታ ያድናል ። ኗሪው ሕዝቧ በአንደበት የተሞላ ከመሆኑም ሌላ ለተቸገረ  የሚለግስ ፤ የተራበ  የሚያበላ ሕዝብ ነው። ከሌሎች ትላልቅ ከተማ ኗሪወች ጋር ሲያስተያዩአቸውም ደግና መልካም መሆናቸው በትልቁ ጎልቶ ይታያል።

ይህ በእንዲህ ላይ እንዳለ ከአረቦች ጋር ተስማምተው ይኖራሉ በሚለው አባባል ላይ ግን ብዙው ከእውነት የራቀ ሆኖ አግንቸው አለሁ። ለዚህም በርካታ ምክኒያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። አንዱና ዋናው ምክኒያት ፤ በጦር ሜዳ  ተገናኝተው አጥቂና ተጠቂ በመሆናቸው አጥቂወች ደረታቸውን ነፍተው አደባባይ ሲወጡ ተጠቂውች ግን አንገታቸውን ደፍተው ያ በጦር ሜዳ የነበረው ትውልድ ብቻ ሳይሆን አዲስ ትውልድ ሲተካም አጥቂወችን በመጥፎ ዓይን እንዲመለከቷአቸው ያስተምራሉ ። ምንም እንኳ ከሁለት ትውልድ በላይ የሚሆን ጊዜ ቢያልፍም ይህ ጥላቻ እየከረረ እንጅ እየተሻለ አልመጣም። እንዲያውም ሁኒታውን እናሻሽል አለን እያሉ ከሁለቱ ማያከል የሚገቡ መጨረሻ ላይ ነገሩን አባብሰውት ይገኟል። ሰው በህዮቱ እያለ መቸነፍ ስለማይሻ ፡ በኔ በኩል ይህ ቁጣ የተሞላበት የአረቦች አመለካከት ምንም እንግዳ ሆኖ አላገኘሁትም።

ሌላው ምክኒያትም ቤሆን ከዜህ ጋር የተያያዘ ነው። አረቦች እራሳቸውን ችለው ለመተዳደር ሲሞክሩ  ከሃገሪቱ ህግና  ደንብ ጋር ብዙ አለመግባባት ያጋጥማቸዋል ። የሃገሪቱን ባንዴራ ከመስሪያ ቤታቸው ለማውለብለብ አይፈልጉም። በዚህ የተነሳም ከህግ ውጭ ሆነው ስለሚገኙ የፖለቲካ መሪዏችም ሆነ ብዙ ባለመብቶች ገለል አድርገው ይተዋቸዋል ።በዚህም የተነሳ የሚኖሩበት ሰፈርም ሆነ የሚሰሩበት ቦታ ተገቢ እንክብካቤ አያገኝም።

ይች በተፈጥሮ የተዋበች ከተማ  የተቋቋመችባት መሬት ገና አረቦችም ሆነ  ይሁዲያውያን ከመፈጠራቸው በፊት የተፈጠረች ምድር ናት ። ለወደፊትም እነዚህ ሃይማኖቶች ሲጠፉ ምድሯ  ግን ለዘላለም ትኖአራለች ። ስለዚህ በማይረባ ጥላቻ ሃይማኖትን ምክኒያት በማድረግ አንዱ የሌላውን መብት እየቀማ ማሰቃየቱ ጭራሽ የማይገባ ሁኔታ ነው። ሁላችንም ቢሆን ለዘላለም ቁመን አንኖርም ። ለጊዜው ግን በፆታ ፤ በቀለም ፤ በወገን እና በተለያዩ  ዘዴወች አንዱን ከሌላው እየለየን በህዮት ላይ ሳለን በስጋና በነፍሳቸው ጭንቀትን እናሳድራለን።

ከተለያዮ ሐጉሮች ፤ ዜጋና ሃይማኖት የምንወክል ደራሴወች ወደ አንድ ዓመት የሚሆን ጊዜ በወር አንድ ጊዜ ከዚህ  ቲቬሪያ ጎዳና 15 በመባል የሚታወቀው ቤት እሁድ ምሸት በመገናኘት በሃሳብ ስንለዋወጥ ከቆየን በኋላ እዚህ ውጤት ላይ መድረሳችን ትልቅ ተስፋ መሆኑን መዘንጋት አይገባም። ምክኒያቱም መጀመሪያ እንደጠቀስኩት ፡ እኔ  ከአሁን በፊት ከማላውቃቸው ሰዏች ጋር በጋራ ተቀምጨ መጨረሻ ላይ ያየሁትን የሰማሁትን እና ከአሁን በፊት በልጅነቴ ከአጋጠመኝ ጋር አቀነባብሬ እና አዛምጀ ለአንባቢያን አቀርባለሁ የሚል እምነት ጭራሽ አልነበረኝም። በተጨማሪም ይህ ትልቅ ቅሬታ በልባቸው ከተመሰጠባቸው የአረብ ዜጎች ጋር እንዴት ያለ  የጋራ ውይይት ማካሂያድ ይቻላል ? የሚል ሃሳብም ከጭንቅላቴ ገብቶ  ያምሰለስለኝ ነበር። በእርግጥ መጨረሻ ላይም ቢሆን ጥሩ ጓደኛሞች  ሁነን ተለያየን ብል ሃሰት እንጅ እውነት አይደለም ።

ዓመቱን በሙሉ ፈራሁ ተባሁ እና ምን ይሉኝ በሚል ሁኔታ በተሞላበት የውይይት መድረክ ላይ ቆይተናል ። ብዙ አለመግባባት ላይም ደርሰናል ። ሆኖም ግን እነኝህ አለመግባባቶች ሁላችንም ቢሆን የተለያየን መሆናችን እንድናውቅ እረድተውናል ።

ታሪክና ምሳሌ አዋቂ ስወች " ሰው ወደመቃብር እስኪገባ ድረስ ከሚያውቀው የማያውቀው ይበዛል " ይላሉ ።እኔም እንደዚህ ። ምንአልባት ለወደፊቱ የዚህ ዓይነት ዕድል ቢያጋጥመኝ ምን ማድረግ ዕንደሚገባኝ ግልፅ ሁኖ  ይታየኛል።

በዚህ አጋጣሚም የውይይት ባልደረቦቸን በሙሉ ሳላመሰግን አላልፍም ።

להשאיר תגובה

הזינו את פרטיכם בטופס, או לחצו על אחד מהאייקונים כדי להשתמש בחשבון קיים:

הלוגו של WordPress.com

אתה מגיב באמצעות חשבון WordPress.com שלך. לצאת מהמערכת /  לשנות )

תמונת גוגל

אתה מגיב באמצעות חשבון Google שלך. לצאת מהמערכת /  לשנות )

תמונת Twitter

אתה מגיב באמצעות חשבון Twitter שלך. לצאת מהמערכת /  לשנות )

תמונת Facebook

אתה מגיב באמצעות חשבון Facebook שלך. לצאת מהמערכת /  לשנות )

מתחבר ל-%s


<span>%d</span> בלוגרים אהבו את זה: